Dataset Viewer
Auto-converted to Parquet Duplicate
text
stringlengths
140
24k
summary
stringlengths
13
164
ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደው ኢትዮትሬል የተራራ ላይ ሩጫ በሚቀጥለው እሁድ ነሀሴ ሶስት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት እንደሚካሄድ የውድድሩ አዘጋጆች ባለፈው ሀሙስ በጉለሌ የእፅዋት ማእከል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ለሁለተኛ ጊዜ በሚካሄደው ሩጫ ለመካፈል ከሁለት መቶ ስድስት በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ዜጎች ለመሳተፍ የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ አርባ በመቶ የሚሆኑ ከውጭ አገር ዜጎች መሆናቸውን ገልፀዋል። በዋነኛነት ከስፔን፣ ጣልያን፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጃፓን፣ ...
ሁለተኛው ኢትዮትሬል የተራራ ላይ ሩጫ ሳምንት ይካሄዳል
ሰኔ ፲፯ አስራ ሰባት ቀን ፳፻፭ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና ፎሬን ፖሊሲ መፅሄት በእያመቱ በሚያወጣው የወደቁ አገራት ሪፖርት ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር ፌልድ ስቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያ እንደ አለፉት አመታት ሁሉ ዘንድሮው የወደቁ ወይም በመውደቅ ላይ ካሉ ሀያ አገራት መካከል አንዷ ሆና ተመድባለች። የህዝብ ቁጥር ፣ የስደተኛ ቁጥር፣ የህዝብ ብሶት፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ ያልተመጣጠነ እድገት፣ የመንግስት ህጋዊነት፣ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የደህንነት ጥበቃ፣ የሊህቃን መከፋፈልና የውጭ ጣልቃ ገብነት የሚሉ...
በሁለት ሺህ አምስት አም ኢትዮጵያ ከወደቁ አገራት ምድብ ተመደበች
ኢሳት ጥር ሀያ ሁለት ፥ ሁለት ሺህ ዘጠኝ ባለፈው ስድስት ወራቶች ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ ሺ የንግድ ተቋማት የንግድ ፈቃዳቸውን በተለያዩ ችግሮች እንደመለሱ ተገለፀ። እነዚሁ በተለያዩ የንግድ ስራዎች ላይ ተሰማርተ የነበሩ ድርጅቶች ህገወጥ ንግድ መበራከት፣ በከተማዋ እየተካሄደ ያለው የልማት እንቅስቃሴ ደካማ የንግድ ስርአት አንዲሁም የቤት ዋጋ ንረት ከገበያ እንዲወጡ ጫና እንዳደረሰባቸው ማስታወቃቸውን ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። በከተማዋ እየተስተዋሉ ያሉ እነዚህን ችግሮች ተከትሎ በየእለቱ ሰባ የሚሆኑ የን...
በአዲስ አበባ ሺ የንግድ ተቋማት የንግድ ፈቃዳቸውን በተለያዩ ችግሮች መለሱ
ከዚሁ ጋር ተያይዞም እቃ አቅራቢው ገቢው ከአምስት መቶ ሺ ብር በላይ ቢሆንም እንኳን ታክሱን የመክፈል ግዴታ የሌለበት ሲሆን የካፊቴሪያ ወይም የምግብ ቤት አገልግሎት የሚሰጠው ሰው ግን ገቢው ከአምስት መቶ ሺ ብር በላይ ከሆነ ለታክሱ የመመዝገብ ግዴታ እና ታክሱን የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል። ከላይ የቀረበው ድንጋጌ የተወሰደው ተጨማሪ እሴት ታክስ በኢትዮጵያ በሚል ርእስ በሳሙኤል ታደሰ ተዘጋጅቶ በግንቦት ወር ሁለት ሺህ አራት አመተ ምህረት ለአንባቢያን ከቀረበው መፅሀፍ ነው። የተጨማሪ እሴት ታክስ ...
ታክስ፤ የህግ፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የአካውንቲንግ እውቀትን ይጠይቃል
ነሀሴ አስራ ሰባት ቀን አመተ ምህረትኢሳት ዜናበኢትዮጵያ የፕትርክና ታሪክ አወዛጋቢ የሆኑት ብፁወ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የመንግስት ባለስልጣናት እና ሌሎች ዲፐሎማቶች በተገኙበት ዛሬ በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን የቀብራቸው ስነስርአት ተፈፅሟል።ከሀምሌ ቀን አመተ ምህረት ጀምሮ ኛ አመት በአለ ሲመታቸውን ሲያከብሩ የነበሩት አቡነ ጳውሎስ በድንገት ማረፋቸው የብዙዎች መነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ ነው። በተለይም የእርሳቸውን ሞት ተከትሎ የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ይፋ መሆን ኢትዮጵያውያን ነገሩን ከሀይማኖ...
የብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስርአት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈፀመ
ብዙውን ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮትም ሆነ በጋዜጦችና መፅሄቶች የሚተላለፉና የሚወጡ ትዝብቶች ወይም አስተያየቶች በአብዛኛው በታዋቂ ግለሰቦች በምሁራን አለያም በፖለቲከኞች ይጣበባሉ። እንደ እኔ ያለው ጭቁን የገጠር መምህር ግን እንዲህ ያለው እድል ብዙም አይገጥመውና እንዲሁ እድሌን ልሞክር ብዬ ነው ይህን ፅሁፍ መላኬ። ለሚዲያ ቢሆን ብዬ ስፅፍም የመጀመሪያ ጊዜዬ ነው። እድሜ ለአበበ ቢቂላ ይሁንና ከእሱ ጊዜ ጀምሮ አትሌቶቻችን በመላው አለም ታውቀው አሳውቀውናል። አበበ ቢቂላ በአለም የውድድር መድረክ አሸንፎ ...
ለአትሌቲክስ ውጤታማነት አዲሱን አመራር ተስፋ እናደርጋለን
በእንግሊዝ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ በጋምቤላ ክልል በተከናወነ አስገዳጅ የሰፈራ ፕሮግራም፣ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ደርሶብኝ፣ ለስደት ተዳርጊያለሁ ያሉ አንድ ኢትዮጵያዊ ገበሬ፤ በአገሪቱ ላይ የመሰረቱትን ክስ ያዳመጠው የለንደን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች ለሚጥሱ ፕሮግራሞች መዋል አለመዋላቸው እንዲጣራ መወሰኑን የኢትዮጵያ መንግስት ተቃወመ። ብሉምበርግ ኒውስ ከትናንት በስቲያ እንደዘገበው፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ለንደ...
መንግስት የእንግሊዝ እርዳታ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ለመጣስ ስለመዋሉ መጣራቱን ተቃወመ
በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በጊዜያዊነት ወደ ጃንሜዳ ተዛውሮ የቆየው አትክልት ተራ በቋሚነት አገልግሎት እሚሰጥበት ወደ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ መዛወሩንና በዛሬው እለት ታሀሳስ ሰባት ቀን ሁለት ሺህ አመተ ምህረት የማፅዳት ስራ እንደሚከናወን የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። ጃንሜዳ ለመጪው ለጥምቀት በአል እንዲደርስ፣ ስፖርታዊና ሌሎች ማሀበራዊ አገልግሎቶችን መስጠት እንዲችል በዛሬው እለት ከጠዋቱ ፡ ሰአት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ወጣቶች፣ የፅዳት ባለሙያዎች ጨም...
የጃንሜዳ ጊዜያዊ አትክልት ተራ ወደ ሀይሌ ጋርመንት የማዘዋወሩ ስራ ተጠናቀቀ
ቻይና በሀገሪቱ ዋና ዋና ቦታዎች ላይ ብሄራዊ የሆኑ የሳይንስ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት እንቅሰቃሴ መጀመሯን አሰታውቃለች።በተለይም በመሰረተ ልማት ግንባታው ዘርፍ ከሀገሯ አልፋ በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር በትብብር በመሰራትም ላይ ትገኛለች ።በሳይንሰ እና ቴክኖሎጂው ዘርፍም ቢሆን የምታደርገው እንቅስቃሴ ከፍተኛ እንደሆነ ይነገራል። አሁን ደግሞ ሀገሪቱ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ቀመሰ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ቆርጣ መነሳቷን የሀገሪቷ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡይገኛሉ።የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን በመጠ...
ቻይና ሳይንሳዊ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሯ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂዮ ሜሎኒ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በታላቁ ቤተ መንግስት የክብር የእራት ተጋብዘዋል። በተጨማሪም ሚኒስትሯ ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እና ከሶማሊያ ...
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ የነበራቸውን የስራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም ሁለት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ፍርድ ቤቱ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያን በማስፋፋት ወንጀል በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ እንዲችል ለፖሊስ ቀናት ፈቀደ። የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮውን ለፖሊስ የፈቀደው የተሰሩና ቀሪ የምርመራ ስራዎችን እንዲሁም የተጠርጣሪዎችን የመከራከሪያ ነጥብ መርምሮ ነው። ተጠርጣሪዎቹ የፀሀይ ሪል ስቴት ጀነራል ማናጀር ኪያ ዦንግን ጨምሮ ዘጠኝ የውጭ ሀገር ዜ...
የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በማተምና ጥቁር ገበያ በማስፋፋት በተጠረጠሩት ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተፈቀደ
አዲስ አበባ፣ ታሀሳስ ሶስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የቴክኒክና ሙያ አሰላሳይና ሀሳብ አመንጪዎች ቡድን ቲንክ ታንክ ግሩፕ በአዲስ አበባ በይፋ ተመስርቷል። የስራና ክሀሎት ሚኒስትር ሙፈሪሀት ካሚል በምስረታው ላይ እንዳሉት፥ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ለውጥ እንዲመጣ በእውቀት፣ በጥናትና ምርምር መደገፍ ያስፈልጋል። ለዚህም አዳዲስ አሰራሮች ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚፈልቁበትን አሰራርና አደረጃጀት መፍጠር ይገባል ብለዋል። በዛሬው እለት የተመሰረተው የቴክኒክና ሙያ አሰላሳይና ሀሳብ አመንጪዎች ቡድንም ጥሩ ጅም...
የቴክኒክና ሙያ አሰላሳይና ሀሳብ አመንጪዎች ቡድን ተመሰረተ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት ሀያ ዘጠኝ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጃራ አባገዳ ትምህርት ቤት ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ህንፃዎች የግንባታ ስራ ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ። ለተከታታይ ሶስት አመታት ሲጠየቅ የቆየውን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ የጃራ አባገዳ ትምህርት ቤት ውስጥ የተማሪዎች መማሪያ፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ የላይብረሪና የላብራቶሪ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች ናቸው የሚገነቡት። ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የህዝብ ጥያቄ ከነበረባቸው አን...
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የጃራ አባገዳ ትምህርት ቤት ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ህንፃዎች የግንባታ ስራ የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ
የፌስ ቡክ ተከታዮቹ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆነዋልቃና ቴሌቪዠን የተመልካቾቹን የመዝናኛ አማራጭ ለማጎልበት ሁለት አዳዲስ ዝግጅቶችን አንድ ወጥ እና አንድ በአማርኛ የተመለሰ ማቅረብ መጀመሩን ገለፀ። በአሁኑ ጊዜ ጣቢያው በየሳምንቱ የስላሳ ሰአት አዳዲስና ያልታዩ ዝግጅቶችን ለተመልካቹ እንደሚያቀርብ በላከው መግለጫ አስታውቋል።ሰሞኑን አምስትኛ ክፍሉ የተሰራጨው የ ምንድን ዝግጅት፣ የተለያዩ ወቅታዊ ማህበረሰብ ተኮር ርእሶችን እያነሳ ከተለያዩ ምልከታዎች አንፃር የሚያወያይ ሲሆን በዚህም የተመልካቾችን ተሳትፎ...
ቃና ሁለት አዲስ ዝግጅቶችን ማስተላለፍ ጀመረ
ኢሳት ዲሲሚያዚያ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር ዛይድ ራድ አል ሁሴን የኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብትን በማክበር ለዜጎች ተስፋ እንዲሰጥ ጠየቁ።ኮሚሽነሩ በኢትዮጵያ ያካሄዱትን ጉብኝት ካጠናቀቁ በኋላ በሰጡት መግለጫ አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አመራር ለህዝቡ የሰጠውን ተስፋ በመተግበር የሰብአዊ መብቶች ሊጠበቁ ይገባል ብለዋል።በጉብኝታቸውም የፖለቲካ እስረኞች የነበሩ ሰዎችን የሀይማኖት አባቶችንና ባህላዊ መሪዎችን አነጋግረው ህዝቡ በአዲሱ አስተዳደር የተገቡ ተስፋዎች መክነ...
የህወሀት አገዛዝ የሰብአዊ መብትን በማክበር ለዜጎች ተስፋ እንዲሰጥ ተጠየቀ
ዜጐች ወደተለያዩ አገሮች ሄደው እንዲሰሩ የሚፈቅደው አዲሱ የግል ሰራተኞችና አሰሪ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ቢፀድቅም አዋጁ ማሟላት ያለባቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ ጉዞው አሁኑኑ አይጀምርም ተባለ። ጉዞው መቼ እንደሚጀመር የተጠየቁት የሰራተኛና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሸለመ፣ አዋጁ ታኀሳስ ቀን ሁለት ሺህ ስምንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቢፀድቅም በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ስላልወጣ፣ የአዋጅ ማስፈፀሚያ፣ አደረጃጀት መመሪያና ደንብ መውጣት ስላለበትና ተጓ...
የውጭ አገር የስራ ስምሪት አዋጅ ቢፀድቅም አሁኑኑ ጉዞ አይጀመርም ተባለ
አቶ አንዱአለም ተፈራ ከገዢው መደብ የምንለይበት በሚል ርእስ ባስነበቡን ፅሁፍ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግስት የሚለውን አጠራር ለምን እንደመረጡ ያስረዳሉ። መጠሪያው ለወያኔ የማይገባው በመሆኑና አቶ አንዱአለም መጠሪያውን ለመጠቀም ያአስቻለኝ ብለው ያቀረቡት ምክንያት በቂና ተገቢ ሆኖ ስላልተሰማኝ ይህችን አስተያየት ፃፍሁ። ትግሬ ስንል የኢትዮጵያ አንድ ክፍል በሆነው ትግራይ የተወለዱና ትግረኛ ቋንቋ የሚናገሩ ወይንም የወላጆቻቸው ስር ከዛ ሆኖ የትም ይሁን የት የተወለዱና ቋንቋውን ሊናገሩም ላይ...
ወያኔን የትግሬ ነፃ አውጪ ማለት ያለ ግብሩ ስም መስጠት
የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፤ ባለፈው ረቡእ ለሶስት ሰአታት በፖሊስ ጣቢያ ታስረው መፈታታቸው ተገለፀ። ዶክተር ነጋሶ፤ ፓርቲው ነገ ያካሂዳል ተብሎ ለሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ካሰማራቸው አባላት ጋር በተያያዘ ታስረው እንደነበር ታውቋል። ባለፈው ረቡእ የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቅሳ ሲያደርጉ የነበሩ የፓርቲው አባላት የቅስቀሳ ፈቃድ የላችሁም ተብለው በፖሊስ መያዛቸውን የገለፀው ፓርቲው፤ የአንድነት ልሳን ጋዜጣ ፎቶግራፍ አንሺም በራሪ ወረቀት ሲቀበሉ የነበሩ ሰዎችን ያለፍላጐ...
ዶክተር ነጋሶ ለሶስት ሰአት ታስረው ተፈቱ
ኢሳት ዜናጥቅምት በቅርቡ ስልጣን በለቀቁት በአቶ በረከት ስምኦን ንብረቶች ላይ የተጀመረው የሙስና ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገለፁ።በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነባው ደብል ትሪ ሆቴል ጋር በተያያዘ የተጀመረው ምርመራ ሙሉ በሙሉ የሆቴሉ ግንባታ የገንዘቡ ምንጭ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን አረጋግጧል።ይህም የተፈፀመው በአቶ በረከት ስምኦን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነት ግዜ እንደሆነ መረጋገጡን ምንጮቹ ጨምረው ገልፀዋል።በአቶ በረከት ስምኦን ንብረቶች ላይ የተጀመረው ...
በአቶ በረከት ስምኦን ንብረቶች ላይ የተጀመረው የሙስና ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ
የአባዲ ሀዲስ እድሜ እያነጋገረ ነው በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ስላሳ አንድኛው ኦሊምፒያድ ከተጀመረ ስድስተኛ ቀን አስቆጥሯል። ከተለያዩ የአለም አገሮች የተሰባሰቡት ስፖርተኞች በተገኙበት የዘንድሮው የሪዮ ኦሊምፒክ ጨዋታ ሀምሌ ሀያ ዘጠኝ ቀን ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት በድምቀት ሲከፈት፣ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በዋናተኛው አቤል ኪሮስ መሪነት ወደ ስታዲየም ሲገባ አቀባበል ተደርጎለታል። ኢትዮጵያ በወርቃማ ውጤቷ የምትታወቅበት የረዥም ርቀት ሩጫ ከነገ በስቲያ አርብ ነሀሴ ስድስት ቀን በሚካሄደው ...
የሴቶችና የወንዶች አስር ሜትር አርብና ቅዳሜ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ሁለት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀድያ ሆሳእና እና አዳማ ከተማ ሶስትለ ሶስት በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል። ጥሩ ፉክክር በታየበት በዚህ ጨዋታ አዳማ ከተማ ሶስት ለ እየመራ ቢቆይም ሀድያ ሆሳእና ነጥብ መጋራት ችሏል። በጨዋታው የአዳማ ከተማን ሁለት ግቦች ዳዋ ሆቴሳ ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ግብ አዲስ ተስፋዬ አስቆጥሯል። የሀድያ ሆሳእናን ሁለት ግቦች ደግሞ ባዬ ገዛኸኝ ያስቆጠረ ሲሆን ፥ አንዷን ግብ ሰመረ ሀፍተይ ማስቆጠር ችሏል።
የሀድያ ሆሳእና እና የአዳማ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር ሀያ ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ።ፕሬዚዳንቷ ለኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባስተላለፉት መልእክት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል።ዳንኤል አራፕ ሞይ ለኬንያ ነፃነት ያደረጉትን ተጋድሎ ያስታወሱት ፕሬዚዳንቷ፥ በኢጋድ ምስረታ ላይ ጉልህ ስፍራ እንደነበራቸውም አንስተዋል።ፕሬዚዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ ቢያልፉም ለህዝባቸው እና ለአፍሪካ ደህንነት ባደረጉት በጎ ተግባር ሁሌም...
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለኬንያውያን የሀዘን መግለጫ አስተላለፉ
በአዲስ አበባ የዳቦ እጥረት ተከሰተ ዘሀበሻ በአዲስ አበባ ከተማ ዳቦ በበቂ ሁኔታ እየቀረበ እንዳልሆነ ተገለፀ። የከተማው ነዋሪዎች በየዳቦ ቤቱ ዳቦለመግዛት ሲሄዱ ዳቦ አለመኖሩ እየተነገራቸው በተደጋጋሚ እየተመለሱ መሆኑንና ችግሩም እስካሁን እንዳልተቀረፈሰንደቅ ጋዜጣ በጥቅምት ቀን አመተ ምህረት እትሙ ዘግቧል። እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ አንዳንድ ዳቦ መሸጫሱቅ የስራ ሀላፊዎችና ባለቤቶች በተገኘው መረጃ መሰረት በዳቦ መሸጫ መንግስት ከተመነው ዋጋ አንፃር ሲታይ አንድን ዳቦ ለገበያ በማቅረብ የሚገኘው የትር...
ዛሬ ከወጡ ጋዜጦች የተመረጡ ዜናዎች እነሆ።
ኢትዮጵያና ሱዳን የአረብ ሊግን ውሳኔ ተቃውመዋል በህዳሴው ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በአምስት ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ተደራድረው መግባባት እንደሚጠበቅባቸው የተገለፀ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት ከድርድር ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የኢትዮጵያ መንግስት አስታውቋል። እ ኤ አ በሁለት ሺህ በተፈረመው የመርሆ መግለጫ ስምምነት መሰረት፤ ከሰሞኑ አሜሪካና የአለም ባንክ ጣልቃ የገቡበት የድርድር ሂደት መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የህግ አማካሪ አምባሳደር ረታ አለሙ አስረድተዋል። በመርሆ ስምምነቱ አንቀ...
ኢትዮጵያና ግብፅ አምስት ጉዳዮች ላይ ተደራድረው መግባባት ይጠበቅባቸዋል
አዲስ አበባ፣ ግንቦት ሀያ ሶስት፣ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ባለፉት ሀያ አራት ሰአት ውስጥ ሶስት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀያ አራት ሰአት ውስጥ በተደረገው ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ስላሳ ስድስት የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ዘጠኝ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በዚህም በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች አንድሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት ደርሷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎችም ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ዘጠና ዘጠኝኙ ከአዲስ አበባ ...
በኢትዮጵያ ባለፉት ሀያ አራት ሰአታት በኮሮና ቫይረስ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አንድ መቶ ዘጠኝ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል
የኢህአዴግ መስራች አባል የሆኑት ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሀት እና የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ የተናጠል ግምገማቸውን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ እስከቀጣዩ ሳምንት እንደሚያከናውኑ ተጠቆመ። በዚህ ሳምንት ግምገማውን የሚጀምረው የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ ሲሆን፣ በሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ ኦህዴድ ግምገማውን እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል። ኢህአዴግን ከመሰረቱት ፓርቲዎች መካከል በቀዳሚነት የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን በማካሄድ በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል እንዲሁም በፓ...
የህወሀትና የኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴዎች የተናጠል ግምገማቸውን ሊጀምሩ ነው
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ ሀያ ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአፍሪካ ህብረት የሚመራውና ለጊዜው ተቋርጦ የነበረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ እንደሚቀጥል የውሀ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ እንደገለፀውም በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለ ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ከሁለት ሳምንታት በፊት የተቋረጠው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ከሳምንት በፊት ሊቀጥል የነበረ ቢሆንም በሱዳን በኩል በቀረበው ለአንድ ሳምንት የይዘግይልኝ ጥያቄ መሰረት ለአንድ ሳምንት ዘግይቷል። በመ...
ተቋርጦ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዛሬ ይቀጥላል
አስናቀ ፀጋዬ አዲስ አበባ፡ በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። በሀገሪቱ የሚታየውን የሲሚንቶ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አመለከተ። በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የብረታ ብረትና ኬሚካል ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ዱጋሳ ዶንሳ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት ፣ሚኒስቴሩ ከስድስት ወር በፊት በምርትና በአቅርቦት በኩል የተፈጠረውን የሲሚንቶ እጥረት መንስኤ ለማጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ ኮሚቴ አቋቁሞ ሲሰራ...
በሲሚንቶ አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ አሁንም ችግሮች እንደሚታዩ ሚኒስቴሩ አስታወቀ
ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የሶማሌ ክልል ውስጥ በርካታ አሰቃቂ ድርጊቶች ሲፈፀምበት እንደቆየ የሚነገርለት የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ሀላፊ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ። ሀሰን ኢስማኤል ኢብራሂም ሀሰን ዴሬ አብዲ ሞሀመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ የቀድሞው የእስር ቤቱ ሀላፊ ሀሰን ኢስማኤል ኢብራሂም በቅፅል ስሙ ሀሰን ዴሬ ሶማሊያ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሎ ለኢትዮጵያ ተላልፎ በመሰጠቱ ወደ ጅግጅጋ ተወስዷል። ግለሰቡ ክስ ወደ ተመሰረተበት አዲስ አበባ ሊወሰድ እንደሚችልም ተነግሯል። ምንጮች ለቢቢሲ እን...
በሶማሌ ክልል የጄል ኦጋዴን እስር ቤት ሀላፊ ተይዞ ለኢትዮጵያ ተሰጠ
የጣሊያን የፋይናንስ ተቋም የብድር ዋስትና ሰጠ የጣሊያን ግዙፉ ኩባንያ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን፣ ጊቤ አራት ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት እንዲሰጠው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር ሲያካሄድ የቆየው ድርድር ተጠናቀቀ። ሳሊኒ በቅርብ ቀናት ውስጥ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር ስምምነት ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል። ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ያካሄደ በመሆኑ የቴክኒክ ጉዳይ አሳሳቢ እንዳልነበረ ያስታወሱት የሪፖርተር ምንጮች፣ የድርድሩ ማ...
የጊቤ አራት ሀይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግንባታ ድርድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት ሀያ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በጋምቤላ ክልል የእንቦጭ አረም በውሀ አካላት ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው ማሀበረሰብ አባላት በጋምቤላ ክልል ጎግ ወረዳ በሚገኘው የታታ ሀይቅ ላይ የእንቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ አካሂዷል። የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋልዋክ ጋርኮት እንዳሉት በክልሉ በሚገኙ የውሀ አካላት ላይ የእንቦጭ አረም እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከ...
ዩኒቨርሲቲው የእንቦጭ አረም እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል እየሰራ ነው
ፀጋዬ አራርሳፀጋዬ አራርሳ በኢሊባቡር በተፈፀመው ዘግናኝ ዘር ተኮር ግድያ ጀርባ ያለውን እውነት እንድንመረምር ፍንጭ ሰጥቶናል።እንዲህም ብሏልኦነግ እኛ ከኦህዴድ ጋር ያደረግነውን የስልጣን ክፍፍል ስምምነት ኦነግ በቅናት አይን እየተመለከተው ነው። የተቃውሞ ሰልፉንም የጠራው የኦነግ ክንፍ የሆነው ነው ሲል ይፈርጃል።ጥቅምት በ ላይ እኦህዴድ ኦነግን ለመደምሰስ ከህወሀት ጋር ሰርቷል።በ ኦነግ ኦህዴድን ለማጥፋት ከህወሀት ጋር ወግኗል።ወዳጅ ጠላት ጠላትም ወዳጅ እየሆነ ነውይለናል።ጥቅምት ኦነግ የህወሀት አጋር...
ከኤሊባቡር ንፁሀን አማሮች ጭፍጨፋ በስተጀርባ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ታላላቅ ሀይማኖታዊ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የደመራ በአል በዛሬው እለት በመላ አገሪቱ ተከብሮአል። የደመራ በአል ንግስት ኢሌኒ እየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ለመፈለግ የተጠቀመችበትን ደመራ እና የእጣን ጭስ ለመዘከር የሚደረግ ሀይማኖታዊ በአል ነው። የቤተክርስቲያኗ መፅሀፍት እንደሚያመለክቱት ግማደ መስቀሉ በአፄ ዳዊትና በልጃቸው ባአፄ ዘርአያቆብ በአስራ አምስተኛም ምእተ አመት መግቢያ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል። በአዲስ አበባ ዛሬ በተከበ...
የደመራ በአል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በማረሚያ ቤቶች ለመከላከል ይቻል ዘንድ አራት ሺህ የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንደሚለቀቁ አስታወቀ። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉዳዩ ላይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እነዚህ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ የይቅርታ ቦርድ ለሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት አቅርቦ ማስፀደቁን አስታውቀዋል። የሚለቀቁት የህግ ታራሚዎች በቀላል ወንጀል እስከ ሶስት አመት ድረስ ተፈርዶባቸው በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ፣ ...
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በማረሚያ ቤቶች ለመከላከል አራት ሺህ የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንደሚለቀቁ አስታወቀ
ግንቦት ፲፬ አስራ አራት ቀን ፳፻፮ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና ከትናንት በስቲያ ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጭ ከጧቱ አንድ ሰአት ተኩል ላይ ወደ ቢሮአቸው በመግባት ራሳቸውን ከሁለትኛ ፎቅ ወርውረው የገደሉት የስልሳ ሁለት አመቱ ዲፕሎማት አቶ ፍሰሀ ተስፉ ስለ አሟሟታቸው መንስኤ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም። ክሮናካ ዲ ሮማ የተባለው የጣሊያን ጋዜጣ ዛሬ ይዞት በወጣው ሰፊ ዘገባ ዲፕሎማቱ ከመሞታቸው ከሁለት ቀናት በፊት ከስራ ተነስተው ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ተነግሮዋቸው እንደነበር አንዳንድ ...
በጣሊያን ራሳቸውን እንዳጠፉ የተነገረላቸው ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት አሟሟት መንስኤ በውል አልታወቀም
አማርኛ ተናጋሪዎችን የማመናመን የማደህየት የማራቆትና ክልላቸውን እያሳነሱ የማጥፋት እቅድ በህወሀት መርሀግብር ውስጥ የተካተተ ዋና ተግባር እንደሆነ ተገለፀ። አማርኛ ቋንቋንም ማሽመድመድ የዚሁ እቅድ አካል መሆኑ ተዘግቧል።አቶ ገመድህን አርአያ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በህወሀት ፕሮግራም ገፅ አካባቢ አማራ የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ተመልክቷል ብለዋል። አያይዘውም አማራ ማጥፋት የቅስቀሳው ዋና መሳሪያ ቢሆንም የትግራይ ህዝብ አልተቀበለም ብለዋል። ቅስቀሳውን አንቀበልም ያሉ...
አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሀት ፕሮግራም ነው
የአገሪቱ ባለሙያዎችና ድርጅቶች እስከ ሀምሌ ይመዝገቡ ተባለበፌደራል ዋና ኦዲተር ጄነራል በብሄራዊ ባንክና በሌሎችም ተቋማት ለሂሳብ ባለሙያዎችና ለኦዲተሮች የሙያ ፈቃድ የብቃት ማረጋገጫና መሰል የእውቅና አሰጣጥ ስርአት በመሻር ለአዲሱ የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ የሰጠው አዋጅና እሱን ተከትሎ የወጣው ደንብ መተግበር ጀመረ። ለአዲሱ ቦርድ የቦርድ አባላትና የስራ ሀላፊዎች ተሹመውለታል።የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አለማየሁ ጉጆ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት ቦርዱ ለብቻው ተለይቶ በ...
የሂሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮችን የሚቆጣጠር አዲስ ቦርድ ተቋቋመ
ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በስግብግቡ ጁንታ የህወሀት ሀይል ላይ የተደረገው የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ በስኬት መጠናቀቁን አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ፤ የአየር ሀይል በወሰደው እርምጃ በተለያዩ ስፍራዎች ላይ የነበሩ ሮኬቶችን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ማውደም መቻሉን ገልፀዋል።ሮኬቶቹ እስከ ሶስት መቶ ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችሉ በመሆናቸውና በወንጀለኛው ቡድን ሮኬቶቹን የመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ በመቐለና አካባቢዋ በነበረው የከባድ መሳሪያ ማስቀመጫ ላይ የአ...
በህወሀት ሀይል ላይ የተወሰደው የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ በስኬት ተጠናቀቀ ጠቅላይ ሚኒስትር
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ አስር፣ሁለት ሺህ ኤፍ ቢሲ በመዲናዋ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የግለሰብን የኤሌክትሪክ ቆጣሪ ቆርጠው ሀይል አቋርጠዋል የተባሉ ሶስት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ። በክፍለ ከተማው ወረዳ ስድስት ልዩ ቦታው ጨው በረንዳ አካባቢ ተጠርጣሪዎቹ ወደ ግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በመምጣት ቆጣሪ ልናነብና ልንመረምር ነው ካሉ በኋላ የኤሌክትሪክ ቆጣሪውን አይተው ስላሳ ሶስት ሺህ ብር እንደቆጠረ ለ...
ሶስት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለሙያዎች ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ፖሊስ ገለፀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የምሁራን ሚና ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የበይነ መረብ ምክከር እየተካሄደ ነው። ውይይቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል። በውይይቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ፣የውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሽ በቀለን ጨምሮ ከ...
የዲጅታል ዲፕሎማሲውን ለማጠናከር ያለመ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ማእከል ተቋቋመ
ኢሳት ግንቦት ሀያ ሶስት ፥ ሁለት ሺህ ዘጠኝ በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ተጋልጠው የሚገኙ ከሰባት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከቀጣዩ ሰኔ ወር ጀምሮ የሚቀርብላቸው የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ሊያልቅ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ። የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣትና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለእርዳታ ጥሪው የሰጠው ምላሽ አነስተኛ መሆን የእርዳታ አቅርቦቱ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ማሳደሩን ድርጅቱ የድርቁን ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው አዲስ ሪፖርት ገልጿል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና መ...
ለተረጂዎች ሲሰጥ የነበረ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ከሰኔ ወር ጀምሮ ሊያልቅ እንደሚችል ተመድ አሳሰበ
መጋቢት አስራ ዘጠኝ ቀን አመተ ምህረት ኢሳት ዜና ላለፉት ሁለት አመታት ሲካሄድ የቆየው ከቅርብ ወራት ወዲህ ቀዝቀዝ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ዛሬ ቁጥሩ እጅግ ብዙ የሆነ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በአንዋር መስጊድ ተካሂዷል።ሙስሊም ኢትዮጵያዊያኑ አላህ ሰላምን እንዲያመጣ ሲማፀኑ አርፍዷል። የሰላም ሰዎች መሆናቸውን ነጭ ወረቀቶችን በማውለብለብ ያሳዩ ሲሆን ተቃውሞውም ያለምንም የፀጥታ ችግር ተጠናቋል።መንግስት እንቅስቃሴውን በሀይል እንደተቆጣጠረው ሲያውጅ ቢከርምም ዛሬ በአንዋር...
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ
በሱዳን መንግስት እና አማፂያን መካከል የመጨረሻ የሰላም ስምምነት መስከረም ሀያ ሁለት በደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ እንደሚፈረም የሰላም ድርድሩ ሀላፊ ገለፁ። የድርድር ቡድኑ ሀላፊ እና የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት የፀጥታ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት ቱት ጋትሏክ ጥቅምት ሁለት በአውሮፓውያኑ በመንግስት እና በሰላም ድርድሩ ሂደት ውስጥ ባሉ ወገኖች መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት የመጨረሻ ፊርማ የሚደረግበት ቀን ነው ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ገልፀዋል። የሱዳን ባለስልጣናት እና የአማፂ ቡድኖች ጥምረት የሆነው የሱዳ...
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ ከቀናት በፊት ከአንድ አማፂ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ተስማምተዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት ሀያ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ወርሀ ፆሙ ለተፈናቀሉና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የምናደርግበት ሊሆን ይባል ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኩስም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሀይማኖት ተናገሩ። ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የአቢይ ፆም መግባትን አስመልክተው ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልእክታቸውም በ...
ወርሀ ፆሙ ለተፈናቀሉና በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የምናደርግበት ሊሆን ይገባል ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
አዲስ አበባ፣ጥር ዘጠኝ፣ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የከተራና የጥምቀት በአል ተሳታፊዎች በአሉን ሲያከብሩ ርቀታቸውን በመጠበቅ ፣ ከንክኪ በመቆጠብ ፣ በተደጋጋሚ እጃቸውን በማፅዳት እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ሳያወልቁ በመንቀሳቀስ ሊሆን እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ። ሚኒስቴሩ ለክርስትና እምነት ተከታዮች፥ ለከተራና ለጥምቀት በአል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፏል። ሚኒስቴሩ በመልእክቱ የከተራና የጥምቀት በአል በምእመናን በብዛት የሚታጀብና አካላዊ ንክኪው እና ጥግግቱ የጠነከረ በመ...
የከተራና የጥምቀት በአል ተሳታፊዎች በአሉን ሲያከብሩ ርቀታቸውን በመጠበቅና ከንክኪ በመቆጠብ ሊሆን እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጠ
ሶስት መቶ ሰባ አምስት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የውሀና መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለበትን ወቅታዊ የግንባታ ደረጃ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት የግድቡ ሲቪል ስሰራዎች በአሁኑ ወቅት የዋናው ግድብ የሲቪል ስራዎች ሰማኒያ በመቶ ተጠናቋል፤ የሀይል ማመንጫዎች የሲቪል ስራ በአማካይ ስልሳ ስድስት በመቶ ተጠናቋል፤ የጎርፍ ማስተንፈሻ የሲቪል ስራዎች ዘጠና ዘጠኝ በመቶ ተጠናቋል፤ የኮርቻው ግድብ ስራዎች ዘጠና ሶስት በመቶ ተጠናቋል የስዊች...
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁን ያለበት ደረጃ ይፋ ሆነ
ከግማሽ ቢሊዮን በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጎንደር ከተማ ውሀ ፕሮጀክት በተመረቀ በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት አቆመ።ኢሳት ዜና ሚያዝያ ቀን አመተ ምህረት ለዘመናት በከፍተኛ የውሀ እጥረት ችግር ተጠቂ ከሆኑት የኢትዮጵያ ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው የጎንደር ከተማን የውሀ ችግር ከ በመቶ ወደ መቶ በመቶ ከፍ ያደርገዋል በዘላቂነትም የከተማዋን የውሀ ችግር ይፈታል የተባለለት የውሀ ፕሮጀክት በተመረቀ በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት በማቆሙም ህዝቡ ለከፍተኛ ችግ...
ከግማሽ ቢሊዮን በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጎንደር ከተማ ውሀ ፕሮጀክት በተመረቀ በጥቂት ወራት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት አቆመ።
End of preview. Expand in Data Studio

Dataset Name

Amharic news dataset

Dataset Details

It is a non-normalized version of news dataset crawled from Amharic news websites and from researchers provided in their works.

Dataset Description

The dataset is collected from different news websites and from different researchers crawled Amharic news dataset from different NLP downstream tasks. News sites like FanaBC, EthiopianReporter, Zehabesha,Esat Amharic, BBC Amharic are the sources for these news data. Tasks like news classification and summarization are the related NLP applications where some of the data in this dataset are used from.

  • Curated by: Dawit K.
  • Language(s) (NLP): Amharic
  • License: MIT

Uses

The dataset can be use in the area of NLP/AI/Data science to build models, improve or finetune previously built models.

Out-of-Scope Use

Please use this data only for research and educational purpose only.

Dataset Structure

The dataset has two fields namely "Text" and "Summary" which can also be "Article" and "Headline" or "Content" and "Title" as per your need of naming the fields. The dataset has three splits as "train", "test", and "eval" (validation) with as percentage split of 80:10:10 respectively.

Dataset Creation

Curation Rationale

The dataset is intended to be used in the task of news summarization and reverse summarization (News article generation).

Source Data

The data is prepared from Amharic news websites.

Data Collection and Processing

After the data is collected from different sources, different stages of processing are done on it. primarily the data gets integrated and filtered null rows, duplicates and removed none amharic scripts. so, in this dataset there are only Amharic/ge'ez scripts to make easy for the model on bias issues. the other processing tasks are abbreviation expansion, and Normalization. This data is the normalized version where all homophones and unliablized letters are as written on the news websites. the non-normalized version of this dataset is available at this Dataset

Recommendations

Users should be made aware of the risks, biases and limitations of the dataset.

Downloads last month
6